Free 30-Day Open Test Drive: You are exploring this academy as a guest learner without sign up!
Sign In / Register
Grade 1
Grade 1 Preview

You are previewing Grade 1 curriculum. Ready to explore all grades and choose your plan?

Sign in to access all the other grades

Course & Lessons

Access EOTC courses, read lessons, take quizzes, and generate AI outlines.

Free Test Drive Mode • Currently Viewing Grade 1

Sign in to access all the other grades & choose your plan

You are experiencing our interactive Grade 1 curriculum sample. Register now to choose your family or church subscription plan and unlock all courses, interactive quizzes, exams, and teacher support.

Sign in to access all the other grades
ABN-001Grade: ALL

Abinet Timihrt (የአብነት ትምህርት)

60 Minutes Session

ትምህርት ፩: መግቢያ፦ ግእዝ የኢትዮጵያ የታሪክና የሥልጣኔ መቅረዝ (ሥርዓተ ንባብ ዘግእዝ)

Classroom Presentation & Zoom
🏛️ ትምህርተ አብነት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Classical Abinet Education) | ክፍል ፩፡ ንባብ ቤት

መግቢያ፦ ግእዝ የኢትዮጵያ የታሪክና የሥልጣኔ መቅረዝ

Introduction: Ge'ez — The Lampstand of Ethiopian History & Civilization

Comprehensive foundations of the Sacred Ge'ez Language, fidel taxonomy, pronunciation canons, and the complete taxonomy of Ge'ez Liturgical Readings (ዐበይትና ንኡሳን ንባባት).

📜

የግእዝ ቋንቋ ታሪካዊ መሠረትና ሁለንተናዊ ፋይዳ

Historical Foundation & Universal Significance of Ge'ez

የግእዝ ቋንቋ ለኢትዮጵያ የሥልጣኔ፣ የታሪክና የሃይማኖት ዋና አምድ ነው። «ግእዝ» የሚለው ቃል በትርጓሜው የመጀመሪያ ወይም ቀዳማይ ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህም ቋንቋው በኢትዮጵያ ምድር ካሉ የጽሕፈት ሥርዓቶች ሁሉ ቀዳሚ መሆኑን ያመለክታል። በተጨማሪም «አግዓዚ» ከሚለው ቃል ጋር በመያያዝ ነፃ ወይም የነፃ ሕዝቦች ቋንቋ የሚል ጥልቅ ትርጉም ይይዛል።

ይህ ቋንቋ ከብዙ ሺህ ዓመታት በላይ የዘለቀ የጽሑፍ ታሪክ ያለው ሲሆን፣ በተለይም በአክሱም ሥልጣኔ ዘመን የአናባቢና የተነባቢ ሥርዓት (አቡጊዳ

  • Abugida) አሟልቶ በመያዝ ለኢትዮጵያ ሴማዊ ቋንቋዎች ሁሉ እንደ እናትና እንደ ጀርባ አጥንት ሆኖ አገልግሏል። ቋንቋው የአገሪቱ ሁለንተናዊ ማንነት የተገነባበት የድንጋይ ማዕዘን ነው። ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የረቀቀ ሥልጣኔ፣ የንግሥና ታሪኳንና ከዓለም ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለትውልድ ያበረከተ የታሪክ መዝገብ ከመሆኑም በላይ፣ ዛሬ ለምንጠቀምባቸው ለብዙዎቹ የአገራችን ቋንቋዎች የቃላትና የሰዋስው ምንጭ በመሆን ለሥነ-ጽሑፋችን ልዩ ውበትን አላብሷል።

ከዚህም ባሻገር፣ ሕዝቡ ለዘመናት ሲመራባቸው የኖሩት የፍትሕ ሥርዓቶች፣ የሥነ-ከዋክብትና የሕክምና ጥበቦች፣ እንዲሁም ማኅበራዊ ወጎችና ዕሴቶች በሙሉ በዚሁ በግእዝ ቋንቋ ተጽፈውና ተቀርጸው የቆዩ በመሆናቸው፣ ግእዝ የኢትዮጵያ የታሪክ ትንሳኤ፣ የሥልጣኔዋ ፋና፣ የማንነቷ መቅረዝ እና የባህላዊ እሴቶቿ ሁሉ ማኅደር ነው። ባጭሩ ግእዝ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ገጽታ የቀለሟ ማድመቂያ፣ የታሪኳ ድርና ማግ፣ እንዲሁም ለዘመናዊ ሥልጣኔዋ መነሻ የሆነ የዕውቀት መጋዘን በመሆኑ፣ ቋንቋውን ማወቅ ማለት የኢትዮጵያን ጥንታዊና ታላቅ ማንነት ከመሠረቱ መረዳት ማለት ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያውያን በሙሉ ልንማረውና ልናውቀው የሚገባ የታሪካችን መሠረት ነው።

The Four Pillars

ግእዝ ለኢትዮጵያ፦ አራቱ መሠረታዊ አዕማድ

Ge'ez for Ethiopia: The Four Pillars of Nationhood

፩

የታሪኳ መሠረት

The Foundation of History

ኢትዮጵያ ከዓለም ጥቂት ከሚባሉ የራሳቸው የጽሑፍ ታሪክ ካላቸው አገራት አንዷ የሆነችው በግእዝ ምክንያት ነው።

  • የመረጃ ምንጭ፦ ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ቦታዎች፣ ስለ ነገሥታቱ የንግሥና ታሪክ፣ ስለ ጦርነቶችና ስለ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች የሚናገሩ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች፣ ብራናዎችና የሳንቲም ላይ ቅርጾች የተመዘገቡት በግእዝ ነው።
  • ቀጣይነት፦ ግእዝ ባይኖር ኖሮ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት በቃል ብቻ ተወስኖ ይቀር ነበር። ግእዝ ግን ታሪካችንን በጽሑፍ ሰድረን ለትውልድ እንድናስተላልፍ አድርጎናል።
፪

የውበቷ መሠረት

The Foundation of Beauty

የግእዝ ቋንቋ የኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍና የጥበብ ጌጥ ነው።

  • የቃላት ውበት፦ ግእዝ እጅግ ረቂቅና ጥልቅ ትርጉም ያላቸው ቃላት ያሉት ቋንቋ ነው። ለምሳሌ በግእዝ ቅኔያት ውስጥ የሚታየው የሰምና ወርቅ ምስጢር የቋንቋውን ውበትና ጥልቀት ያሳያል።
  • የፊደላት ንድፍ፦ የግእዝ ፊደላት ራሳቸው ለዓይን የሚማርኩ፣ በሥዕላዊ ቅርጻቸው የታነፁና ለሥዕልም ሆነ ለጌጣጌጥ ሥራዎች (Calligraphy) እንደ ውበት ምንጭ የሚያገለግሉ ናቸው።
፫

የባህሏ መሠረት

The Foundation of Culture & Tradition

የአንድ ሕዝብ ማንነት የሚገለጸው በባህሉና በሥርዓቱ (ወጉ) ነው።

  • ማኅበራዊ ዕሴቶች፦ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የጋብቻ፣ የቀብር፣ የንግሥና እና የበዓላት ሥነ-ሥርዓቶች አብዛኞቹ የሚከናወኑት ከግእዝ መጻሕፍትና ትውፊቶች ነው።
  • ሥነ-ምግባር፦ ግእዝ የሕዝቡን የኑሮ ዘይቤ፣ የእንግዳ ተቀባይነትንና የአብሮነትን ዕሴት የሚገልጹ በርካታ የጥበብ መጻሕፍትን ይዟል። «ወግ» ሲባል የቆየው የሕዝብ አኗኗር ሥርዓት ተጠብቆ የኖረው በዚህ ቋንቋ አማካኝነት ነው።
፬

የሥልጣኔዋ መሠረት

The Foundation of Civilization

ሥልጣኔ የሚለካው በሕግ፣ በሥነ-ጽሑፍ፣ በሕንፃ ጥበብና በዕውቀት ክምችት ነው።

  • የሕግ ሥርዓት፦ ኢትዮጵያ ለዘመናት ስትመራበት የነበረው «ፍትሐ ነገሥት» የተጻፈው በግእዝ ነው። ይህ ደግሞ አገሪቱ የዳበረ የፍትሕ ሥርዓት እንደነበራት ያሳያል።
  • ዕውቀት (ሳይንስና ፍልስፍና)፦ የሥነ-ከዋክብት (ባሕረ ሐሳብ)፣ የሕክምና መጻሕፍት፣ እና የረቀቁ የፍልስፍና ሥራዎች (ሐተታ ዘዘርዐ ያዕቆብ) ግእዝ የሥልጣኔ ቋንቋ መሆኑን ያረጋግጣሉ።
  • አርክቴክቸር፦ ከአክሱም ሐውልቶች እስከ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ድረስ ያሉት ቅርሶች የጌጥና የምህንድስና መመሪያዎቻቸው በግእዝ የተቃኙ ናቸው።

«ግእዝ» የሚለው ቃል ሦስት ዋና ዋና ትርጓሜዎች

Three Fundamental Linguistic & Philosophical Definitions of "Ge'ez"

  1. 1የመጀመሪያ (ቀዳማይ)

Primary / First Order

በግእዝ ፊደል አቆጣጠር የመጀመሪያው ቤት (ለምሳሌ፦ 'ሀ') ግእዝ ይባላል። ይህም ቋንቋው የመጀመሪያውና የቀደመው መሆኑን ያመለክታል።

  1. 2ነፃ (አግዓዚ)

Free / Unconquered Spirit

ግእዝ ማለት ነፃ የወጣ ወይም ነፃነት ማለት ነው። ይህም ቋንቋው የነፃ ሕዝቦች ቋንቋ መሆኑንና ከሌሎች ቋንቋዎች ተፅዕኖ የጸዳ መሆኑን ይገልጻል።

  1. 3ተፈጥሮ (ባሕርይ)

Nature / Inherent Character

የሰው ልጅ ማንነት፣ ጠባይ ወይም ተፈጥሮአዊ ቋንቋ (Natural/Primal Language)። በጥንታዊ ሥነ-ጽሑፍ «ግዕዙ የዋህ ነው» ሲባል ጠባዩ ገር ነው ማለት ሲሆን፤ የሰው ልጅ የተፈጠረበት ቀዳሚ ድምፅ ተደርጎ ይታመናል።

የግእዝ ቋንቋ ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞች (Benefits of Ge'ez)፦

🏺 የታሪክና የዕውቀት ምንጭ

የጥንታዊ ሕክምና፣ የሥነ-ከዋክብት (አቡሻኽር)፣ የሕግና የታሪክ ድርሳናት ማኅደር።

🌿 የዘመናዊ ቋንቋዎች መሠረት

ለአማርኛ፣ ለትግርኛና ለኢትዮ-ሴማዊ ቋንቋዎች ሁሉ እንደ እናት ቋንቋ ማገልገሉ።

⛪ መንፈሳዊና ሊተርጂካዊ ዕሴት

የቅዱስ ያሬድ ዜማ፣ የቅዳሴ ምስጋናዎችና የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ቅርስ ምንጭ።

💡 ፍልስፍናና ሥነ-ጽሑፍ

እንደ ሐተታ ዘዘርዐ ያዕቆብ ያሉ ዓለም አቀፍ የፍልስፍና ጥበቦች መገኛ መሆኑ።

ሦስቱ መሠረታዊ የንባብ ደረጃዎች (Three Stages of Literacy)

The Classical Pedagogical Stages of Nibab Bet Recitation

ደረጃ ፩ (Stage 1)

የግእዝ (ማጋዝ) ንባብ

Elemental / Syllabic Recitation

«ማጋዝ» ማለት አንድን ነገር ተሸክሞ ቀስ በቀስ መጓዝ ማለት ነው። የተለያየ ቅርጽ፣ ስያሜና ድምፅ ያላቸውን ሆሄያት በማገናኘት ቃልን መመሥረት፤ ተማሪው ፊደላቱን በዝግታና በጥንቃቄ እየቆጠረ በማንበብ ለቀጣዩ ደረጃ መሠረት ይጥላል።

ደረጃ ፪ (Stage 2)

ውርድ ንባብ

Continuous / Flowing Cadence

የተቆጠሩትን ቃላት እርስ በእርስ በማያያዝ እንደ ውሃ ፈሳሽ አወራርዶ ማንበብን ያመለክታል። የቃላቱ ድምፅ ሳይቆራረጥና ሳይሰነጠቅ፣ የኀዘኒታ ስሜት ባለው የዜማ ስልት በተለይም በሰሙነ ሕማማት፣ በስቅለትና በቅዳሜ ስዑር አገልግሎት ላይ ይውላል።

ደረጃ ፫ (Stage 3)

ቁም ንባብ

Standing / Masterful Articulation

የንባብ የመጨረሻ ደረጃ ነው። የድምፅ ቃናውን፣ የዜማ ስልቱንና የሥርዓተ ነጥቦቹን ሕግ ጠብቆ በተረጋጋ ሁኔታ በፍጥነትና በቅልጥፍና ማንበብ ነው። የት ጋር መቆም፣ መሳብና ማረፍ እንዳለበት ጠብቆ ቃላትን በማንሣትና በመጣል የሚቀርብበት የሊቃውንት ንባብ ነው።

ሥርዓተ ንባብ ዘግእዝ፦ ፳፮ቱ (26ቱ) የግእዝ ፊደላትና ቅጥያዎቻቸው

The 26 Primary Ge'ez Consonants and the 7 Phonetic Orders

፩. ጥንታዊው የቀዳማይ ቅደም ተከተል (Ancient Abjad Order)

1. አ 2. በ 3. ገ 4. ደ 5. ሀ 6. ወ 7. ዘ 8. ሐ 9. ኀ 10. ጠ 11. የ 12. ከ 13. ለ 14. መ 15. ነ 16. ዐ 17. ፈ 18. ጸ 19. ፀ 20. ቀ 21. ረ 22. ሰ 23. ተ 24. ጰ 25. ፐ 26. ሠ

፪. የዘመናዊው ንባብ ቤት ቅደም ተከተል (Standard Liturgical Order)

1. ሀ 2. ለ 3. ሐ 4. መ 5. ሠ 6. ረ 7. ሰ 8. ቀ 9. በ 10. ተ 11. ኀ 12. ነ 13. አ 14. ከ 15. ወ 16. ዐ 17. ዘ 18. የ 19. ደ 20. ገ 21. ጠ 22. ጰ 23. ጸ 24. ፀ 25. ፈ 26. ፐ

የ26ቱ ፊደላት ሰባቱ ቅጥያዎች (The 7 Orders Matrix)

Ge'ez • Ka'eb • Salis • Rabi' • Hamis • Sadis • Sabi'
1st (ግእዝ) 2nd (ካዕብ) 3rd (ሣልስ) 4th (ራብዕ) 5th (ሐምስ) 6th (ሳድስ) 7th (ሳብዕ)
ሀሁሂሃሄህሆ
ለሉሊላሌልሎ
ሐሑሒሓሔሕሖ
መሙሚማሜምሞ
ሠሡሢሣሤሥሦ
ረሩሪራሬርሮ
ሰሱሲሳሴስሶ
ቀቁቂቃቄቅቆ
በቡቢባቤብቦ
ተቱቲታቴትቶ
ኀኁኂኃኄኅኆ
ነኑኒናኔንኖ
አኡኢኣኤእኦ
ከኩኪካኬክኮ
ወዉዊዋዌውዎ
ዐዑዒዓዔዕዖ
ዘዙዚዛዜዝዞ
የዩዪያዬይዮ
ደዱዲዳዴድዶ
ገጉጊጋጌግጎ
ጠጡጢጣጤጥጦ
ጰጱጲጳጴጵጶ
ጸጹጺጻጼጽጾ
ፀፁፂፃፄፅፆ
ፈፉፊፋፌፍፎ
ፐፑፒፓፔፕፖ

ጎደሎ (ዲቃላ) ሆሄያት (Labiovelars)

5-Order Labiovelar Consonants (ግእዝ፣ ሣልስ፣ ራብዕ፣ ሐምስ፣ ሳድስ)

1st (ግእዝ) 3rd (ሣልስ) 4th (ራብዕ) 5th (ሐምስ) 6th (ሳድስ)
ቈቊቋቌቍ
ኈኊኋኌኍ
ኰኲኳኴኵ
ጐጒጓጔጕ

ተመሳሳይ ድምፅና ልዩ ትርጉም ያላቸው ሆሄያት

Homophones with Distinct Morphological Names

ሃሌታው ሀ

ሐመሩ ሐ

ብዙኃኑ ኀ

ንጉሡ ሠ

እሳቱ ሰ

አልፋው አ

ዐይኑ ዐ

ጸሎቱ ጸ

ፀሐዩ ፀ

💡 ምሳሌ፦ መሀረ = አስተማረ (Taught) | መሐረ = ይቅር አለ፣ ማረ (Forgave)

Sacred Recitation Canons

የግእዝ ንባባት (ዐበይትና ንኡሳን)

The Complete Taxonomy of Ge'ez Liturgical Readings

፩. ዐበይት ንባባት (The 4 Major Reading Categories)

  1. 1ተነሽ (Teneš) • 2. ሰያፍ (Seyaf) • 3. ተጣይ (Tetay) • 4. ወዳቂ (Wedaqi)

ቀይ = ተነሽና ሰያፍ (High Pitch) አረንጓዴ = ተጣይና ወዳቂ (Low Pitch)
፩. ተነሽ (Teneš) ድምፅን ከፍ በማድረግ (Rising Pitch)

ተነሽ ንባብ

ድምፅን ከፍ በማድረግ ትእዛዛዊ በሆነ መልኩ ወይም ደግሞ ድምጽን ቆጣ በማድረግ ይነበባል። አንድ ተነሽ ቃል በሚነበብበት ጊዜ የመጨረሻው ሆሄ (ፊደል) ይነካል ወይም ይረገጣል (ይጠብቃል)። ተነሽ ቃላት በግእዝ (1ኛ)፣ በካዕብ (2ኛ)፣ በሣልስ (3ኛ)፣ በራብዕ (4ኛ) ወይም በሳብዕ (7ኛ) ፊደል ሊጨርሱ ይችላሉ። በሐምስና በሳድስ ፊደል አይጨርሱም!

ግእዝ (1st) ካዕብ (2nd) ሣልስ (3rd) ራብዕ (4th) ሳብዕ (7th)
ገጽየ ይሄሉ ለኪ ኢየኀይድዋ ያግዕዞ
ስምእየ ወይትዋሐዱ ተፈሥሒ ወይብልዋ ንሰብሖ
ንስእለከ ወፈነዎሙ ወልድኪ ንወድሳ ያግብኦ
፪. ሰያፍ (Seyaf) ድምፅን ከፍ በማድረግ (Slanted Accent)

ሰያፍ ንባብ

ሰያፍ ንባባት ልክ እንደ ተነሽ ድምፅን ከፍ በማድረግ ይነበባሉ። ነገር ግን የመጨረሻው ፊደል አይነካም፤ ከመጨረሻው ፊደል በፊት ያለው ፊደል ይነካል ወይም አጽንኦት ይሰጠዋል። ሰያፍ ቃላት በሳድስ (6ኛ) ፊደላት ብቻ ይጨርሳሉ (ከ«ዝ» በስተቀር)። በመጽሐፍ በቀይ ቀለም ተጽፈው በሳድስ የሚጨርሱ ቃላት በሙሉ ሰያፍ ናቸው።

የሰያፍ ቃላት ምሳሌዎች (Seyaf Examples)፦

አአትብ

A'atəb

ጽዮን

Ts'əyon

ይመጽእ

Yəmäts'ə'
፫. ተጣይ (Tetay) ድምፅን ዝቅ በማድረግ (Dropped/Low Pitch)

ተጣይ ንባብ

ድምፅን ዝቅ በማድረግ በትሑት መልክ ይነበባሉ። ተጣይ ቃላት ልክ እንደ ሰያፍ የሚጨርሱት በሳድስ (6ኛ) ፊደል ነው። በተጨማሪም የመጨረሻውን ፊደል አይነካም። በዚህ መጽሐፍ ተጣይና ወዳቂ በአረንጓዴ ቀለም ተጽፈዋል። በአረንጓዴ ተጽፎ በሳድስ ካለቀ ተጣይ ይሆናል።

የተጣይ ቃላት ምሳሌዎች (Tetay Examples)፦
አምላክ Amlak
ቅዱስ Qəddus
ሰላም Sälam
፬. ወዳቂ (Wedaqi) ድምፅን ቀዝቀዝ በማድረግ (Falling/Calm Tone)

ወዳቂ ንባብ

ልክ እንደ ተጣይ ድምፅን ቀዝቀዝ በማድረግ ይነበባል። ልዩነታቸው በተጣይ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል አይነካም፤ በወዳቂ ጊዜ ግን የመጨረሻው ፊደል ይነካል ወይም ይረገጣል። ወዳቂ ቃላት በሰባቱም ቅጥያዎች (ግእዝ፣ ካዕብ፣ ሣልስ፣ ራብዕ፣ ሐምስ፣ ሳድስ፣ ሳብዕ) ሊጨርሱ ይችላሉ።

ግእዝ ካዕብ ሣልስ ራብዕ ሐምስ ሳድስ ሳብዕ
አሐተ አሐዱ ማሕየዊ ውዳሴሃ ሥላሴ ጠቢብ እግዚኦ
በህየ ከማሁ ከይሲ ሕማማ ጊዜ ብፁዕ አልቦ
ተሥዓተ ሎቱ ብእሲ ጸጋ ውዳሴ ህልው ኵሎ

፪. ንኡሳን ንባባት (The 6 Minor Reading Modulations)

The Six Sacred Phonetic Marks and Articulation Principles

፩ (1) ነቁጥ (Dot Under)

የሚጠብቅ

Geminated / Stressed Syllable

የሚጠብቀውን ፊደል አጥብቆ ማንበብ ማለት ነው። የነቁጥ ምልክት « » ከስራቸው ያለባቸው ቃላት ጠብቀው ይነበባሉ።

ምሳሌ፦ ገጽየ ፣ እምየ

፪ (2) ያለ ነቁጥ (No Dot)

የሚላላ

Soft / Unstressed Syllable

ሳይጠብቅና ሳይረገጥ ላልቶ የሚነበብ የንባብ ዓይነት ነው።

ምሳሌ፦ ስምከ ፣ ዘለከ ፣ አቡነ ፣ ሲሳየ

፫ (3) በሁለት ነጥብ « ፡ »

ተናባቢ

Liaison / Connected Breath

ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ቃላትን በአንድ ትንፋሽ ሳያርፉ በማያያዝ የሚነበቡ ናቸው።

ምሳሌ፦ ቅድሳተ ስብሐቲከ ፡ ለመስቀለ እግዚእነ ፡ ወበእንተ መድኃኒትነ

፬ (4) ተነጥሎ (Separate)

ኢተናባቢ

Disjoint / Standalone Word

አንድ ቃል ከሚከተለው ቃል ጋር ሳይያያዝ ራሱን ችሎ የሚነበብ ነው።

ምሳሌ፦ ንገኒ ለከ ፣ አሐዱ አምላክ ፣ በቅድስት ሥላሴ

፭ (5) ቀስት/ቀስት መሰል « »

የሚጠቀልል

Elided / Swallowed Consonant

ፊደሉ ተውጦ ወይም ተጠቅሎ ይነበባል ማለት ነው። « » ይህ ምልክት ፊደሉ ተጠቅልሎ የሚነበብ መሆኑን ያመለክታል።

ምሳሌ፦ ዘንተ ፣ ወትረ ፣ ምድር ፣ መጽአ ፣ ጥንቁቀ

፮ (6) ተቆጥሮ (Counted)

የሚቆጥር

Metered / Distinctly Counted

ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ከስራቸው የሌለባቸው ቃላት እያንዳንዱ ፊደል ተቆጥሮ ይነበባል።

ምሳሌ፦ ሠጠጠ ፣ ሞገሰ ፣ ረከበ ፣ ኀደረ ፣ ወረደ

Visual Hierarchy Tree

የግእዝ ንባባት መዋቅር (Ge'ez Readings Hierarchy Flowchart)

Exact reproduction of the sacred pedagogical classification tree

የግእዝ ንባባት ዐበይት ንባባት ንኡሳን ንባባት ተነሽ ሰያፍ ተጣይ ወዳቂ የሚጠብቅ የሚላላ ተናባቢ ኢተናባቢ የሚጠቀልል የሚቆጥር
🔑

ቁልፍ (Key)

Essential Liturgical Decoders for Readers & Chanting Students

🔴

ተነሽና ሰያፍ ቃላት

· ተነሽና ሰያፍ ቃላት በቀይ ቀለም ተጽፈዋል። በሳድስ የሚጨርሱት ሰያፍ ናቸው። በቀይ ተጽፎ በሳድስ ፊደል ያልጨረሰ ቃል ሁሉ ተነሽ ንባብ ነው።

🟢

ተጣይና ወዳቂ ቃላት

· ተጣይና ወዳቂ በአረንጓዴ ቀለም ተጽፈዋል። በአረንጓዴ ተጽፈው በሳድስ ፊደል የሚጨርሱ ቃላት ተጣይ ሲሆኑ በሳድስ ፊደል ካልጨረሱ ደግሞ ወዳቂ ናቸው።

🔗

ተናባቢ ቃላት

· ተናባቢ ቃላት “:” በዚህ ምልክት ተለይተዋል። በዚህ መካከል የተጻፉ ሁሉ በአንድ ትንፋሽ ተያይዘው ይነበባሉ።

🎯

የሚጠብቁ ፊደላት

· የሚጠብቁ ፊደላት ከስራቸው “.” ይህ ምልክት አለባቸው። አለበለዚያ አይጠብቁም ማለት ነው።

💫

የሚዋጡ ቃላት

· የሚዋጡ ቃላት ደግሞ ከስራቸው “” ይህ ምልክት አለ። አለበለዚያ ተቆጥረው ይነበባሉ ማለት ነው።

«ጥበብ ሰረቀት እምጽዮን
  • Wisdom Dawned from Zion!»

EthioWisdomSchool

  • Classical Ecclesiastical Excellence & Liturgical Literacy

🎥 የንባብ ሥርዓት ማስተማሪያ ቪዲዮ (Ge'ez Reading Audio-Visual Guide)
Teacher's Classroom Log & Reflections2019 ዓ.ም. (2026–2027)

የመምህር ዕለታዊ ማስታወሻና የክፍል መዝገብ (Document Today's Teaching)